loading
በፒያሳ የሚገኘዉ የዳግማዊ አፄ ምኒሊክ ሀውልት እድሳት ተጠናቀቀ::

ለስድስት ወራት በእድሳት ምክንያት ተሸፍኖ የቆየዉ ሀዉልትም በሚቀጥለዉ ሳምንት ለህዝብ ይፋ ይሆናል ተብሏል፡፡
የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የህዝብ ግኑኝነት ዳይሬክተር አቶ ወርቁ መንገሻ ለአርትስ ቲቪ እንደተናገሩት የቅርስ እድሳቱ ከሴባስቶፖል መድፍ ጋር 5 ሚሊዮን ብር ፈጅቷል ፡፡
ዳይሬክተሩ ለሃውልቱ እድሳት የተያዘለት የዘጠኝ ወር ግዜ ቢሆንም ቀድሞ በስድስት ወር ጊዜ ዉስጥ እድሳቱ እንደተጠናቀቀ ተናግረዋል፡፡
እድሳቱ በአዲስ አበባ ባህል እና ቱሪዝም ፣ በኢትዮጲያ ቅርስ ጥናት እና ጥበቃ ባለስልጣን እንዲሁም በ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጋራ ተከናውኗል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *