loading
የአራት ማረሚያ ቤቶች አስተዳዳሪዎች ከሃላፊነታቸው ተነሱ፡፡

ከሃላፊነታቸው የተነሱት የቂሊንጦ ፤ የቃሊቲ፤ የሸዋ ሮቢት እና የድሬዳዋ ማረሚያቤቶች አስተዳዳሪዎች መሆናቸዉን አርትስ ቲቪ ለማወቅ ችሏል፡፡
የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ረዳት የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ አዲሱ ጴጥሮስ ለ አርትስ እንደለፁት፤ በቅርቡ ታራሚዎች በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ከፍተኛ የሠብዓዊ መብት ጥሠት እንደሚፈፀምባቸው በመናገራቸዉ እና ማረሚያ ቤቱም አስተዳዳሪዎቹ ጋር ችግር እንዳለ በማረጋገጡ ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ ተደርጓል፡፡
የቃሊቲ ከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ቤት ዳይሬክተር ገብረኢየሱስ ገብረ እግዚአብሄር ፣ የቂሊንጦ ቀጠሮ ማረሚያ ቤት አስተዳደር ዋና ሱፐር ኢንተንደንት አሰፋ ኪዳኔ፣ የሸዋ ሮቢት ማረሚያ ቤት ሃላፊ ዋና ሱፐር ኢንተንደንት የማነ አስፋው እንዲሁም የድሬዳዋ ማረሚያ ቤት ዳይሬክተር መኮንን ደለሣ ከስልጣን ተነስተው በአዳዲስ አመራሮች ተተክተዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *