loading
በምህረት አዋጅ ሰበብ በማረሚያ ቤቶች ተከስቶ የነበረዉ አለመረጋጋት መስከኑን የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር አስታወቀ ፡፡

የምህረት አዋጁ ከወጣ በኋላ ምህረት ይገባናል በሚል በተለያዩ ማረሚያ ቤቶች ሁከት ተከስቶ እንደነበርና አሁን ግን በማረሚያ ቤቶች ዉስጥ መረጋጋት መፈጠሩን የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ረዳት የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ አዲሱ ጴጥሮስ ለአርትስ ቲቪ ተናግረዋል፡፡
አቶ አዲሱ በጠቅላይ አቃቤ ህግ የምህረት አዋጁ ዝርዝር አፈፃፀም መሰረት በምህረቱ ተጠቃሚ የሚሆኑ እና ተጠቃሚ የማይሆኑ ታራሚዎች በግልፅ ይፋ ከሆነ በኋላ እንዲሁም የፌደራል ማረሚየ ቤቶች አስተዳደር ባደረገው ውይይትና ስለምህረት አዋጁ በሰጠዉ ግንዛቤ መረጋጋት ተፈጥሯል ብለዉናል፡፡
አቶ አዲሱ መረጋጋቱን ተከትሎም ማረሚያ ቤቶቹ ወደ መደበኛ ስራቸው መመለሳቸውን እና የታራሚ ቤተሰቦች ታራሚዎችን መጠየቅ ጀምረዋል ብለዋል፡፡ ሰላም ከሰፈነባቸዉ ማረሚያ ቤቶች መካከል ቂሊንጦ፣ ቃሊቲ እና ሸዋ ሮቢት ይገኙበታል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *