loading
የ ኮድ 3 አጋዥ ታክሲ ባለቤቶች በሰልፍ አቤቱታ እያቀረቡ ነው ።

“ጥያቄአችን ካልተመለሰ ስራ እናቆማለን” ብለዋል ። በአዲስ አበባ ከተማ በአጋዥ ታክሲ ትራንስፖርት አግልግሎት ላይ የተሰማሩ ኮድ 3 ሚኒባስ ተሽከርካሪ ባለንብረቶች 22 አካባቢ በሚገኘው የአዲስ አበባ መንገድ ትራንስፖርት ፅህፈት ቤት ፊትለፊት አቤቱታ ለማቅረብ ስራ አቁመው ተሰልፈዋል። የተቃውሞው መነሻ “የተተመነው የታክሲ ታሪፍ ከተሰጠን ስምሪት ርቀት ጋር ባለመጣጣሙ ለኪሳራ እየዳረገን ስለሆነ ይሻሻልልን” የሚል ነው። በአሁኑ ሰአት በመቶዎች የሚቆጠሩ ታክሲዎች በፅህፈት ቤቱ በር ላይ ተሰልፈው የሚታዩ ሲሆን ወደመገናኛ የሚሄደው አስፓልት መንገድም በዚህ ሳቢያ በመዘጋቱ የትራፊክ ፍሰቱ ተስተጓጉሏል። “ታክሲዎች የስራ ማቆም አድማ እያደረጉ ነው” መባሉን ተከትሎ ስለሰልፉ አላማ ያነጋገርናቸው ባለንብረቶች “አቤቱታ እያቀረብን እንጂ የተቃውሞ ሰልፍ እያደረግን” አይደለም ይላሉ። ” ጥያቄያችንን እየጠየቅን እንጂ የስራ ማቆም አድማ እያደረግን አይደለም። መብትን ለመጠየቅ መሰለፍ አድማ ሳይሆን መብት ነው ። መብታችንን እንደምታዩት በስርአትና በህጋዊ አግባብ እየጠየቅን ነው። ጥያቄያችን ካልተመለሰ ግን እየከሰርን መቀጠል ስለማንችል ስራ ለማቆም እንገደዳለን” ብለዋል። ባለንብረቶቹ ገና አቤቱታ ላይ በመሆናቸው ከፅህፈት ቤቱ ስለተሰጣቸው ምላሽ ለማወቅ አልተቻለም

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *