loading
ናይጄሪያ የሰብል ምርት እጥረት አሳስቧታል።

በአፍሪካ በህዝብ ብዛቷ ቀዳሚ የሆነችው ናይጄሪያ በየዓመቱ ስድስት መቶ ሚሊዮን ቶን ሩዝ ለምግብ ፍጆታ ታውላለች።
ሲ ጂቲ ኤን እንደዘገበው ከዚህ ውስጥ ግማሽ ያህሉን የምታስገባው ከቻይና ነው ። የናይጀሪያ የግብርና ተማራማሪዎች በሃገሪቱ ያለውን የምርት እጥረት ለመፍታት ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው።
ተማራማሪዎቹ ከቻይና የተሻሻለ የሩዝ ዝርያ በማስገባት አርሶ አደሮቹን ምርታማ ለማድረግ ነው እየሰሩ ያሉት።
የተሻሻለው ዝርያ ቀድሞ ከነበረው ጋር ሲወዳደር የአስራ አምስት በመቶ የምርት ጨማሪ ማሳየቱንም ተመራማሪዎቹ ደርሰንበታል ብለዋል።
ምርምሩ ከዘጠኝ ዓመት በላይ የፈጀ ሲሆን ከአምስት መቶ በላይ የሩዝ ዓይነቶች በምርምሩ ስራ ለሙከራ አገልግሎት ውለዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *