loading
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሀጅ ተጓዦች ላይ የተፈጠረውን የበረራ መስተጓጎል ችግር ለመቅረፍ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ከትላንትናው ዕለት ጀምሮ የሀጅ ተጓዦች በረራቸው ተሰርዞ በአየር መንገድ ውስጥ ያለ በቂ ምግብና ማረፊያ እየተጉላላን ነው ብለዋል፡
ይህን ተከትሎ አቢሲ ወደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ስልክ ደውሎ ስለ ሁኔታው ለማጣራት ቢሞክርም አየር መንገድ ስለ ጉዳዩ በፌስ ቡክ ገፁ ካወጣው መረጃ ተጨማሪ የሚሰጠው መረጃ እንደሌለው የህዝብ ግንኙነት ክፍል አስታውቋል፡፡
አየር መንገዱ በፌስ ቡክ ገፁ ባወጣው መግለጫ በሀጅ ተጎዦች ላይ የበረራ ጉዞ መስተጓጎል መፈጠሩን አመልክቷል፡፡
ይሁንጂ ችግሩ የተፈጠረው የሀጂ አስተባባሪ ኮሚቴው ተጨማሪ ተጓዥ በመላኩና በሶማሌው ባለው ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ ምክንያት ከጅግጅጋ የሚመጡ ተጓዦች በመዘግየታቸው መሆኑን አስታውቋል፡፡
ከጉዞው ለተስተጓጎሉት የሀጅ ተጓዦች በረራው እስኪስተካከል በነበራቸው ቆይታ የምግብና ማረፊያ ቦታ ማዘጋጀቱንም አመልክቷል፡፡
አየር መንገዱ ተጨማሪ በረራ በማዘጋጀት የሀጅ ተጓዦቹን እንደሚያመላልስ አስታውቋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *