loading
በ2019 የታዳጊዎች አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ እየተሳተፈ የሚገኘው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የጅቡቲ አቻውን በሰፊ የግብ ልዩነት አሸነፈ፡፡

በማጣሪያው የመጀመሪያ ጨዋታው የኡጋንዳ ቡድንን 1 ለ 0 ማሸነፉ የሚታወስ ሲሆን በሁለተኛ ጨዋታው ጅቡቲን 4 ለ 0 በመርታት ወደ ተከታዩ ደረጃ ለማለፍ የሚያደርገውን ጉዞ አሳምሯል፡፡
የቀይ ቀበሮዎቹን የድል ጎሎች በየነ ባንጃ፤ በረከት ካሌብ፤ ቢንያም አይተን፤ መንተስኖት እንድርያስ አስቆጥረዋል፡፡
እዚሁ ምድብ ኬንያ ደቡብ ሱዳንን 4 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
በቀጣይ መጭው እሁድ ነሃሴ 13 በቻማዚ ኢትዮጵያ ከ ደቡብ ሱዳን እና በመጨረሻ ረቡዕ ነሃሴ 16 ኢትዮጵያ ከ ኬንያ ይጫወታሉ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *