loading
የዘንድሮ አረፋ በዓል በአዲስ አበባ በአንድነት በአንድ ቦታ በስቴዲም ይከበራል፡፡

በነገው ዕለት የሚከበረው ዒድ አል አድሃ አረፋ ከሌሎች ግዜያቶች በተለየ መልኩ በአንድነት እና በፍቅር ስሜት እንድሚከበር ነዉ የአድስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክርቤት ፕሬዝደንት ሼህ መሀመድ ሸሪፍ ሃሰን ለአርትስ ቲቪ የተናገሩት፡፡
የዘንድሮው አረፋ ልዩነታችን ተገፎ በአንድነት እና በእርቅ ማከበራችን ለየት ያደርገዋል ብለዋል፡፡
በዓሉም ‹ሰላም እና አንድነት ለኢትዮጵያ›› በሚል መሪ-ቃል እንደሚከበርም ሼህ መሀመድ ነግረዉናል፡፡
የ አረፋ በዓል ሰላምን እና አንድነትን የምናንፀባርቅበትን እንዲሁም እርስ በእርስ ይቅር የምንባባልበት ከመሆኑም በላይ ከዚህ በፊት ባልተለመደ መልኩ ተበታትኖ የሚሰግድዉ ህዝበ ሙስሊም ነገ በአነድነት በአዲስ አበባ እስታዲየም እንደሚሰግድ ተናግረዋል፡፡
በዘንድሮው የአረፋ በዓልም የእስልምና ሃይማኖት መሪዎች ሚኒስተሮች እና አምባሰደርችን ጨምሮ
ሁለት ሚሊዮን ሙስሊም በስቴዲየም ተገኝቶ በዓሉን ያከብራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *