loading
በነገው እለት የሚከበረውን የአሸንዳ በአል አስመልክቶ በመቀሌ ከተማ የፓናል ውይይት ተካሂዷል።

የፓናል ውይይቱ አብይ አላማ ያለፉት አመታት የበዓሉን አከባበር መገምገም፣አሸንዳን በአለም አቀፍ ደረጃ ስለማስተዋወቅ እንዲሁም ከዩኔስኮ ጋር የተያያዙ ጥናቶች እና ሀሳቦችን ማንሳት ነው ተብሏል፡፡
የትግራይ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ሃላፊ ወ/ሮ ዘነቡ ሐለፎም እንደገለፁት አሸንዳ ከባህላዊ እና ሃይማኖታዊ አንድምታው በተጨማሪ ለሴቶች ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ትስስር እንዲሁም ፖለቲካዊ ተሳትፎአቸውን የሚያሳይ የነጻነት ቀን ነው ብለዋል፡፡
በውይይቱ የቀደሙ የአሸንዳ ባህል አከባበርን የሚያሳይ የፎቶግራፍ አውደ ርእይም ተካሂዷል።
ወ/ሮ ዘነቡ ኤርትራዊያን በበዓሉ እንደሚታደሙ ገልጸው በክብረ በዓሉ ስራዎቻቸውን ለማቅረብ ኤርትራዊያን አርቲስቶች ትላንት መቀሌ እንደገቡ ለአርትስ ተናግረዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *