loading
ጋዜጠኞችን የደበደቡ የዩጋንዳ ወታደሮች የእስር ትእዛዝ ወጣባቸው፡፡

የሀገሪቱ ወታደራዊ አዛዥ ጄኔራል ዴቪድ ሙሁዚ ጸጥታ የማስከበር ስራን ሽፋን አድርገው ጋዜጠኞችን በጭካኔ የደበደቡ ወታደሮች ላይ ከባድ ቅጣት እንዲተላለፍባቸው ጠበቅ ያለ ትእዛዝ አስተላልፈዋል፡፡
የኬንያው ደይሊ ኔሽን ጋዜጣ እንደዘገበው ጋዜጠኞቹ ባለፈው ሰኞ በዩጋንዳ ፖለቲከኞች ይፈቱ የሚል አመጽ ባሰነሱ ሰልፈኞች ላይ የጸጥታ ሀይሎች የሚወስዱትን ርምጃ ሲዘግቡ ነው ድብደባው የደረሰባቸው፡፡
የዩጋንዳ መከላከያ ተቋም ይህን ትእዛዝ ያስተላለፈው በሀገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ዘንድ ከፍተኛ ውግዘት ስለበዛበት ነው ተብሏል፡፡
የዩጋንዳ ወታደራዊ ቃል አቀባይ ሌፍተናንት ኮሎኔል ብሪግ ካርሜር ለተፈጠረው ነገር ሁሉ ይቅርታ አንጠይቃለን ወደፊትም ከየትኛወም ሚዲያ ጋር በቀና መንፈስና በትብብር ለመስራት ዝግጁዎች ነን ብለዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *