loading
ኢንጂነር ታከለ ኡማ በኮየ ፈጬ ሳይት የሚገኙ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የሚገኙበትን ደረጃ ጎበኙ

በምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የተመራውና የከተማ አስተዳደሩ የስራ ኃላፊዎችን ያካተተ ልኡካን በ11ኛው ዙር የተላለፉ የኮዬ ፈጬ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎችን አነጋግረዋል።

ነዋሪዎች የተለያዩ መሰረተ ልማቶች ባለማሟላቱ ቅሬታቸውን ገልጸውላቸዋል በተለይም የውሃ፣ የመብራት  እና የባለድርሻ አካላት በቅንጅት ተናበው አለመስራት በኑሮአቸው ላይ ተጽዕኖ እንደፈጠረ ነው የገለጹት፡፡

ከንቲባ ኢንጂነር ታከለም የሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎች የህብረተሰቡን ቅሬታ ወስደው በአስቸኳይ መፍትሔ እንዲያስቀምጡ ማሳሰባቸውን የአዲስ አበባ ከንቲባ ፅህፈት ቤት በድረ ገፁ አስታውቋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *