loading
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ቁጥር ወደ 30 ለማድረስ እየሰራሁ ነው አለ፡፡

በአሁኑ ወቅት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ቁጥር ስድስት ደርሷል፡፡
የፓርኮቹ መገንባት እና ስራ ላይ መዋል የኢንቨስትመንት ዘርፉን ውጤታማ እንደሚያደርግ እና አሁን ካሉት ስድስት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ወደስራ የገቡ እና በቅርቡ ስራ የሚጀምሩ መኖራቸውን በኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ተካ ገብረ እየሱስ ተናግረዋል፡፡
የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ጥቅምት 2011 ስራ የሚጀምር ሲሆን በቂሊንጦም የመድሃኒት ማምረቻ ኢንዱስተሪ ፓርክ ሊገነባ መሆኑን ሰምተናል፡፡
አቶ ተካ እንደገለፁት ኢንዱስተሪ ፓርኮች በውስጣቸው በርካታ ኩባኒያዎች ያሏቸው በመሆኑ ለአስተዳደራዊ ስራዎች ምቹናቸው ይኸውም ከሙስና የፀዳ አሰራር እና ከፍትኛ ገቢ ማስገኛ ይሆናሉ ብለዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *