loading
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በ2010 በጀት አመት 3.7 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አገኘው አለ፡፡

ይህን ያለው ኢንቨስትመንት ኮሚሽኑ ዛሬ ባቀረበው የአመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ላይ ነው፡፡
የተገኘው ገቢ ባለፈው አመት ከተገኘው የሚያንስ መሆኑን እና የባለፈው አመት ገቢ 4.1 ቢሊዮን እንደነበረ የኢትዮጲያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ በላቸው መኩሪያ ተናግረዋል፡፡
ኮሚሽኑ በበጀተ አመቱ 4.6 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት ያቀደ ቢሆንም 3.7 ቢሊዮን ዶላር ብቻ ነው ገቢ ያረገው
የውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንቶችን መሳብ ፣የመድሃኒት ማምረቻ ኢንቨስትመንት መጀመር፣የኢንዱስትሪ ፓርኮች ወደ ስራ መግባት ኮሚሽነሩ በአመት ውስጥ እንደ ስኬት ያነሱት ሲሆን፤ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ፣የኤሌክትሪክ እና ውሃ አቅርቦት ችግር እንዲሁም በአንዳንድ የሃገሪቱ ክፍሎች የነበረ አለመረጋጋትን ለገቢዉ መቀነስ ምክንያት ናቸዉ ብለዋል፡፡
በአመቱ በኢንቨስትመንት ዘርፍ ቻይና እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ትልቅ ድርሻ እንደነበራቸዉ ተገልጽዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *