loading
በመዲናዋ ምክትል ከንቲባ የሚመራ የውሀና ፍሳሽ ቦርድ ተቋቋመ

በምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ሰብሳቢነት የሚመራ አዲስ የውሀ እና ፍሳሽ ቦርድ መቋቋሙን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።
ዘጠኝ አባላትን ያካተተ ቦርድ ሲሆን፥ የከተማዋን የውሀ ችግር ለመፍታትና በአዲስ አበባ ዙሪያ ከሚገኙ የኦሮሚያ ከተሞች ጋር በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረቱ ነው ተብሏል።
ቦርዱ አዳዲስና ነባር ፕሮጀክቶችን የሚቆጣጠር እና በበላይነት እንደሚመራ ተገልጿል።
በመዲናዋ ያለውን የውሀ ችግር ለመፍታት ፣ ወንዞችን እና ተፋሰሶችን በተገቢው መንገድ ጥቅም ጥቅም ላይ ለማዋል የቦርዱ መቋቋም ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው ተብሏል።
የተቋቋመው ቦርዱ በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙ የኦሮሚያ ልዩ ዞን አመራሮችን እና ከከተማዋ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የተውጣጡ የተለያዩ ባለሙያወች የተካተቱበት ነው።
ኤፍ.ቢ.ሲ

አርትስ 23/12/2010

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *