AfricaPoliticsSocial

ሜርክል በአፍሪካ ስደት ይብቃ እያሉ ነው፡

የጀርመኗ መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል የምዕራብ አፍሪካ ይፋዊ ጉብኝታቸውን በሴኔጋል ጀምረዋል፡፡
ሮይተርስ እንደዘገበው ሜርክል ቀጣይ የጉብኝት መዳረሻዎቻቸው ጋና እና ናይጀሪያ ናቸው፡፡
የሜርክል ጉብኝት ዋነኛ ዓላማ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የቅርብ አጋራቸው ካደረጓት አፍሪካ ጋር ያላቸውን የንግድና የልማት አጀንዳ ለማጠናከር ነው፡፡
የስደተኞች እናት የሚል ቅጽል ስም የተሰጣቸው ሜርክል በአፍሪካ ያለው ስደት እንዲቆም ከተፈለገ ለአህጉሪቱ ወጣቶች ስራ መፍጠር ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር መሆን አለበት ብለዋል፡፡
ይህን ለማድረግ ደግሞ ኢቨስትመንትን ማስፋፋት እና የአህጉሪቱን ዕድገት ማፋጠን የግድ ይላል ያሉት ሜርክል ሀገራቸው ከአፍሪካ ጋር ያላትን የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡

አርትስ 24/12/2010

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button