loading
ኦሜዳድ በ25 ዓመት ውስጥ በመላ ሀገሪቱ 25 ቅርንጫፎችን ከፍቻለው አለ፡፡

ይህንን የሰማነዉ ድርጅቱ 25ኛ ዓመት የብር ኢዮቤልዩ በዓሉን ባከበረበት ወቅት ነው፡፡
ከዉጭ የተለያዩ ምርቶችን በማስገባት የሚታወቀዉ ድርጅቱ ሲቋቋም መነሻዉ 1 ሚሊዮን ብር ካፒታል የነበረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ከ 500 ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል እንዳለዉ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ኩመላ ግራኝ ተናግረዋል፡፡
ባለፉት 25 ዓመታት ጠንካራ እና ትውልድ ተሻጋሪ ድርጅት ለማቋቋም በተሰራው ስራ በርካታ ስኬቶችን ማስመዝገቡን የተናገሩት ደግሞ የድርጅቱ መስራች የሆኑት አቶ ጌታመሳይ ደገፉ ናቸው፡፡
ለዚህም ማሳያ በአዲስ አበባ አንድ ዘመናዊ ሆቴል እያስገነባ መሆኑንና ዱከም ላይ ፋብሪካ ለማስገንባት በዕቅድ ላይ መሆኑን አቶ ጌታመሳይ ተናግረዋል፡፡
ድርጅቱ በበጎአድራጎት ስራ ላይ በመሳተፍ 10 ወላጅ አልባ ህጻናትን ሙሉ ወጪያቸውን በመሸፈን በማስተማር ላይ መሆኑንም ሰምተናል፡፡

አርትስ 24/12/2010

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *