loading
ዛሬ በተካሄደ የ2018/19 የዩሮፓ ሊግ የምድብ ድልድል አርሰናልና እና ቼልሲ ብዙ ርቀቶችን ተጉዘው ጨዋታዎቻቸውን ያደርጋሉ፡፡

አርትስ ስፖርት 25/12/2010
በሞናኮው የምድብ ዕጣ አወጣጥ ስነ ስርአት የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በአሰልጣኝ ኡናይ ኢምሪ እየተመራ የዩሮፓ ሊግ ውድድሩን ሲያደርግ፤ አሰልጣኙ በዩሮፓ ሊግ ያካበቱትን ልምድ በመጠቀም ክለቡን ተጠቃሚ ያደርጉታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ አሰልጣኝ ኡናይ ኢምሪ በስፔኑ ክለብ ሲቪያ ቆይታቸው በተከታታይ ለሶስት ጊዜ የዩሮፓ ሊግ ድልን ማጣጣም ችለዋል፡፡
መድፈኞቹ ባለፈው የኢሮፓ ሊግ ተሳትፏቸው በአርሰን ቪንገር እየተመሩ እስከ ግማሸ ፍፃሜው መጓዝ ቢችሉም፤ በስፔኑ አትሌቲኮ ማደሪድ በድምር ውጤት 3 ለ 2 ተሸንፈው ከውድድሩ መሰናበታቸው ይታወሳል፡፡ በመሆኑም የእርሳቸው የመድረኩ ስኬታማነት እና ልምድ ለአውሮፓ ውድድሮች ስኬታማነት ባይተዋር ሁኖ ለሚገኘው አርሰናል በእጅጉ ይጠቅመዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በዚህም በእጣ አወጣጥ ስነ ስርአቱ አርሰናል በምድብ አምስት ከአዘርባጃኑ ካራባግ፤ ከፖርቹጋሉ ስፖርቲንግ ሊዝበን እና ከዩክሬኑ ቮርስክላ ጋር ተደልድሏል፡፡
ሌላኛው የለንደን ክለብ የሆነው እና በጣሊያናዊው ማውሪሲዮ ሳሪ የሚሰለጥነው ቼልሲ ጉዞውን ወደ ምስራቅ አውሮፓ እያደረገ ከቤላሩሱ ባቲ ቦሪሶቭ፤ ከሀንጋሪው ቪዲ እና ከግሪኩ ፓኦክ ሳሎኒካ ጋር በመጨረሻው ምድብ 12 ተመድቧል፡፡
ቼልሲ በ2013 የዩሮፓ ሊግን በስፔናዊው አሰልጣኝ ራፋኤል ቤኔቴዝ እየተመራ የፖርቹጋሉን ቤኔፊካ አምስተርዳም አሬና ላይ 2 ለ1 በማሸነፍ ዋንጫውን ማንሳቱ አይዘነጋም፡፡
ከጣሊያናዊው አሰልጣኝ ጋር በፕሪምየር ሊጉ መልካም ጉዞ እያደረጉ የሚገኙት ሰሚያዊዎቹ በኢሮፓ ሊግስ ጥሩ ግስጋሴ ይኖራቸው ይሆን አብረን እናያለን፡፡
በስቴቨን ጄራርድ የሚመራው የስኮትላንዱ ሴልቲክ በምድብ ሁለት ከ ኤፍ.ሲ ሳልዝበርግ፤ አር.ቢ ሌብዝህ እና ሮዘንበርግ ጋር ተደልድሏል፡፡
የጣሊያኑ ኤስ ሚላን ከ ኦለምፒያኮስ፤ ሪያል ቤቲስ እና ዱደላንጌ ጋር ተካቷል፡፡
የ2018/19 የዩሮፓ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ በአዘርባጃን መዲና ባኩ የሚካሄድ ሲሆን የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታዎች እ.አ.አ መስከረም 20/2018 መደረግ ይጀምራሉ፡፡
አርትስ ስፖርት 25/12/2010
በውድድሩ በ12 ምድቦች፤ በአጠቃላይ 48 ክለቦች ይካፈላሉ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *