loading
የ2018 ዳይመንድ ሊግ የፍፃሜ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል::

አርትስ ስፖርት 26/12/2010

ትላንት ምሽት በቤልጂየም ብራስልስ በወንዶች የ5000 ሜ የዓለማችን የጊዜው ጎበዝ አትሌቶች ተገናኝተው የአትሌቲክስ ስፖርት አድናቂዎችን ቀልብ የሰረቀ ድንቅ ፉክክር አሳይተዋል፡፡ በፋክክሩ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ አምስተኛ ያሉትን ደረጃዎች በመያዝ አሸነፊ ሆነዋል :: በዚህ ውድድር ቀዳሚ የሆነው ወጣቱ ሰለሞን ባረጋ ሲሆን ውድድሩን በ12 ደቂቃ ከ40 ሰከንድ በሆነ ጊዜ ሲያጠናቅቅ ከ2013 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ፈጣኑ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
በውድድሩ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ሆነው ያጠናቀቁት ሀጎስ ገብረሕይወት በ12:45.82 እና ዮሚፍ ቀጄልቻ 12:46.79 ናቸው::
ሙክታር እድሪስ 12:55.18 በሆነ ጊዜ አራተኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ በብራስልሱ የዳይመንድ ሊግ የፍፃሜ ውድድር ላይ ተሳታፊ የነበሩት ሌሎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የጨረሱበት ሰዓትም የግል የምንግዜም ምርጡ ሰዓታቸው ሆኖ ተመዝግቦላቸዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *