loading
የፖሊስ አባላቱ ከ 100 ሺህ ብር የህዝብ አደራ ይበልጣል አሉ

አርትስ 26/12/2010
ነሀሴ 23 ቀን 2010 ዓ/ም ከምሽቱ 12፡00 ገደማ፤ በአዲስ አበባ በተለምዶ ጋንዲ ሆስፒታል አካባቢ ከህብረተሰቡ በደረሱ ጥቆማዎች እንዲታሸጉ ከተደረጉ ቤቶች መካከል በአንዱ እንዲህ ሆነ።


በቦታው ላይ የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት የሆኑት ዋና ሳጅን ተክሉ ቶማ እና ሳጅን እሸቱ ሰኢድ በፓትሮል መልክ ጥበቃ ያደርጋሉ፤ አንዲት ሴት ወደ እነርሱ ትመጣለች ከታሸጉ ቤቶች የአንዱ ቁልፍ እንዳላት ትነግራቸዋለች፤ ቤቱን ወይ እኔ ወይ እናንተ ክፈቱትና ውስጥ ያሉትን ብሮችን እናውጣ ስትል 100,000.00 ( መቶ ሺህ ብር ) የእጅ መንሻ ታቀርባለች፤ ፖሊሶቹ በሀሳቧ ይስማማሉ። ነገር ግን ባለቤቱ እንዲመጣ ይነግሯታል፤ የተባለው ግለሰብ ሲፈራ ሲቸር፣ ቢደርስም፤ በቁጥጥር ስር መዋሉ ግድ ነበርና ይኸው ተደርገ፡፡ ቤቶቹ እንዲበረበሩ ተደረገ እግጅ በርካታ ከሦስት መቶ ሺህ ብር በላይ የሀገር ውስጥ ገንዘቦችና አስር ሺዎች የሚጠጉ የውጭ ሀገራት ገንዘቦች ተያዙ፡፡
ለምን የሚል ጥያቄ ቀረበ ‹‹ ፖሊስ ስለሆንን ›› ሲሉ መልሰዋል ‹‹ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሀገርንና የህዝብን ክብር ከፍ ብሎ እንዲታይ አድርገዋል፤ ሁላችንም በተሰማራንበት ሙያ በትጋት በመስራት እናግዛቸው፤ የአዲስ አበባ ህዝብን ይበልጥ ለማገልገል እንተጋለን ብለዋል›› ፖሊስ በሚሊየን የሚቆጠሩ ገንዘቦች በቁጥጥር ስር እየዋለ ነው፡፡


ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *