EconomyEthiopiaPoliticsRegionsSocial

የአንበሳ አውቶብስ ድርጅት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር እንዲሆን ተወሰነ::

አርትስ 28/12/2010
ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ሥልጣን ከተረከቡ በኋላ በወሰዷቸው የተለያዩ የሪፎርም ሥራዎች ወደ ፌዴራል ሄደው የነበሩ መሥሪያ ቤቶችንና አሠራሮችን ለመመለስ በወሰዱት ዕርምጃ፣ አንበሳ አውቶብስ ድርጅት እንዲመለስ ተደርጓል፡፡
የአንበሳ አውቶብስ ድርጅት ቀደም ሲል በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር ይተዳደር ነበር፡፡ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በወሰነው ውሳኔ መሠረት ወደ አዲስ አበባ እንዲመለስ፣ ከዚህ በተጨማሪ በሥሩ ሲተዳደር የቆየው የጅማ ከተማ አንበሳ አውቶብስ ድርጅትም ራሱን ችሎ እንዲደራጅ ተወስኖ ነበር፡፡
ከአዲስ አበባ ከተማ ወደ ፌዴራል መንግሥት እንዲዛወሩ ከተደረጉ ተቋማት ውስጥም የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፣ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለሥልጣን፣ እንዲሁም አንበሳ የከተማ አውቶብስ ድርጅትና ከትራንስፖርት ጋር የተያያዙ የተለያዩ አሠራሮች ተጠቃሾች ናቸው፡፡
ነገር ግን ውሳኔው በተለያዩ መሰናክሎች ተግባዊ ሳይደረግ ቆይቶ፣ በሥራ አመራር ቦርድና በፌዴራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን ሲመራ ቆይቷል፡፡
አዲሱ ካቢኔ ግን የአንበሳ አውቶብስ ድርጅት ወደ አዲስ አበባ ከተማ እንዲመለስ ውሳኔ አስተላልፏል ሪፖርተር እንደዘገበው፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button