loading
ብራዚል በእሳት የወደመብኝን ሙዚየም መልሸ ለመገንባት ድጋፍ እሻለሁ ብላለች፡፡

ብራዚል በእሳት የወደመብኝን ሙዚየም መልሸ ለመገንባት ድጋፍ እሻለሁ ብላለች፡፡

ቢቢሲ እንደዘገበው አፍሪካን ጨምሮ የበርካታ ሀገሮች ቅርሶች በውስጡ ይዞ ለዘመናት የቆየው የብራዚል ብሄራዊ ሙዚየም ከ90 በመቶ በላይ በቃጠሎው ወድሟል፡፡
የብራዚል ፕሬዝዳንት ሚሸል ቴሜር ብሄራዊ ሙዚየሙን እንደገና ለመገንባት ከተለያዩ ኩባንያዎች እና ባንኮች ድጋፍ ያስፈልገናል ብለዋል፡፡
የሀገሪቱ የባህል ሚንስትር ሰርጂዮ ሌይታኦ ኢስታዶ ዲ ሳኦፖሎ ከተባለው ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የቃጠሎው መንስኤ ከኤሌክትሪክ ጋር የተያያዘ መሆኑን ምርመራዎች አመላክተዋል ብለዋል፡፡
ሙዚየሙ 12 ሺህ ዓመት እድሜ ያለው የሰው ቅሪተ አካልን ጨምሮ 20 ሚሊዮን የሚሆኑ ቅርሶች በውስጡ ነበሩበት፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *