loading
በዳውሮ ዞን ኢሰራ ወረዳ በመሬት መንሸራተት የ12 ሰዎች ህይወት አለፈ

አርትስ 29/12/2010

በደቡብ ክልል ዳውሮ ዞን ኢሰራ ወረዳ ዛሬ ማለዳ ላይ በጣለው ከፍተኛ ዝናብ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት የ12 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ አራት ሰዎች ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸዉ የወረዳዉ ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የመሬት መንሸራተቱ በወረዳዉ ጉዛ ቀበሌ ዘማ መንደር በሶስት መኖርያ ቤቶች ላይ መከሰቱን የጽህፈት ቤቱ ኃለፊ ሻምበል አልታዬ አለሙ ገልፀዋል፡፡

በአደጋው ከሞቱት 12 ሰዎች መካከል በህብረተሰቡ ተሳትፎ የ10ሩ አስክሬን የተገኘ ሲሆን፥ የሁለቱ አስክሬን ባለመገኘቱ ፍለጋ እየተካሄደ መሆኑም ተነግሯል፡፡

ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸዉን አራት ግለሰቦች ወደ ተርጫ ሆስፒታል በመውሰድ የህክምና ዕርዳት እንዲያገኙም እየተደረገ ነዉ፡፡

በአደጋዉ ወደ 1 ሚሊየን የሚጠጋ ንብረት የወደመ ሲሆን፥ በቀጣይ ጊዜያትም በስፍራዉ ያሉ ቤቶች ጥንቃቄ ካልተደረገላቸዉ የከፋ ጉዳት ሊደርስ እንደሚችል አመላክተዋል፡፡
ኤፍ.ቢ.ሲ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *