loading
በቻይናዋ ቤጂንግ ከተማ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የቻይና አፍሪካ ፎረም የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቋል።

አርትስ 30/12/2010
ፎረሙ ላይም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ተሳትፈዋል።
በፎረሙ ከተላለፉት ውሳኔዎች ውስጥ አፍሪካ እና ቻይና በቀጣይ 3 ዓመታት ማለትም እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2019 እስከ 2021 በሚኖራቸው የትብብር አቅጣጫ ላይ ውሳኔ የተሰጠ ሲሆን የቤጂንግ ድንጋጌን ከማፅደቅ በዘለለ ድንጋጌውን ለማስፈፀም የወጣውን የድርጊት ስነስርዓት በፎረሙ ላይ ፀድቋል።
በዘንድሮው የቻይና አፍሪከ ትብብር ፎረም ላይ ስምንት የትብብር አቅጣጫዎች ይፋ መደረጋቸውም ተገልጿል።
ሁሉም የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች በቻይና እና በአፍሪካ መካከል ያለው ግንኙነት የበለጠ እንዲጠናከር በአንድ ድምፅ የወሰኑበት ነው ብለዋል።
ከእነዚህም ውስጥ አረንጓዴ ልማት፣ ሰላም እና ፀጥታ፣ አቅም ግንባታ እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ተጠቃሽ መሆናቸውን ታውቋል።
የትብብር አቅጣጫዎቹ የአፍሪካ ህብረት የ2063 እቅድን መሰረት አድርጎ የተቀረፀ መሆኑም በፎረሙ ላይ ተገልጿል።
ጉባዔውን አስመልክቶ የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ፥ ለሁለት ቀናት በቤጂንግ የተካሄደው የቻይና አፍሪካ ትብብር ፎረም ስኬታማ ሆኖ መጠናቀቁን እና የቻይና አፍሪካ ትብብር በዓለም አቀፍ ተለዋዋጭ ሁኔታዎች ቢፈተንም ስኬታማ እና ታሪካዊ ነው ብለዋል።
ኤፍ.ቢ.ሲ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *