loading
የስራ ማቆም አድማ ላይ የቆዩት የዓየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ ገቡ

አርትስ 30/12/2010
ለቀናት የስራ ማቆም አድማ ላይ የቆዩት የዓየር ትራፊክ ተቆጣጣሪ ሰራተኞች ዛሬ ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ ገቡ።
የኢትዮጵያ ሲቪል አቭዬሽን ባለስልጣን ዳይሬክተር ጀነራል ኮሎኔል ወሰንየለህ ሁነኛው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳረጋገጡት፥ ሰራተኞቹ ወደ ስራ ተመልሰዋል።
ከመንግስት በተሰጠ አቅጣጫም በደመዎዛቸው ላይ ማስተካከያ ለማድረግ ጥናት ይካሄዳል ብለዋል።
የሌሎች ሰራተኞችን ፊርማ አስመስሎ በመፈረምና ሌሎች ስራ እንዲያቆሙ በማነሳሳት ወንጀል የተጠረጠሩ ዘጠኝ የሲቪል አቭዬሽን እና የዓየር ትራፊክ ሰራተኞች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወቃል።
ኤፍ.ቢ.ሲ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *