loading
ስለሺ ደምሴ (ጋሽ አበራ ሞላ) የተካተተበት የተፋሰስና አረንጓዴ አከባቢዎች ልማት ቦርድ ተቋቋመ

አርትስ 30/12/2010

ዛሬ የተቋቋመው ቦርድ አስተዳደሩ ከተማዋን እነደ ስያሜዋ ውብ እና ፅዱ ለማድረግ በያዛቸው እቅዶች የሚተገበሩ አዳዳዲሰ ፕሮጀክቶችን ጨምሮ በከተማዋ የሉ ፓርኮችን በበላይነት የሚመራ ይሆናል ተብሏል ፡፡በምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ(ኢንጂነር) ሰብሳቢነት የሚመራው ቦርድ 10 አባላትን ያካተተ መሆኑን ከከንቲባ ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ፡፡
ከአንጋፋ የኪነጥበብ ባለሞያዎች መካከል አበበ ባልቻ፣ መሰረት መብራቴ፣ አቶ ስለሺ ደምሴ (ጋሽ አበራ ሞላ) ፤ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ተሾመ ፍሮምሳ ፤ ከባህልና ቱሪዝም ቢሮ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ ፤ ከኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማህበር ፕሬዝዳንት አርክቴክት መስከረም ታምሩ እና ሌሎችም በአባልነት ተካተዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *