loading
ጂቡቲ በተራዋ እንግዶቿን ተቀብላለች፡፡

አርትስ 01/13/2010
የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት በችግሮቻቸው ዙሪያ በመምከር በአካባቢው ሰላም እንዲሰፍን ጥረታቸውን ቀጥለዋል፡፡
በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ እና የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሰላም ተልእኮ ይዘው ጂቡቲ ገብተዋል፡፡ የሚኒስትሮቹ የጉዞ አላማ በኤርትራ እና በጂቡቲ መካከል ያለውን የድንበር ውዝግብ ለመፍታት ያለመ ውይይት ለማድረግ ነው፡፡
የኤርትራ ፕሬስ የሀገሪቱን የማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀልን ጠቅሶ እንዳስነበበው ሁለቱ ሀገሮች በዱሜራ ደሴት አካባቢ የይገባኛል ጥያቄ ሳቢያ ግንኙነታቸው ሻክሮ ቆይቷል፡፡
ሰሞኑን የሶስቱ ሀገራት መሪዎች አስመራ ላይ በሶስትዮሽ ግንኙነት ላይ ከመከሩ በኋላ የጂቡቲ እና የኤርትራ ጉዳይ እልባት እንዲያገኝ በጋራ ለመስራት ተስማምተው ነበር የተለያዩት፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *