loading
ዛሬ የሚጠናቀቀው የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ማዕከላዊ ኮሚቴ (ኦህዴድ) በሎጎ ለውጥ፣ መዝሙር እና መተዳደሪያ ደንብ ላይ ውይይት እያደረገ ነው

አርትስ 01/13/2010
የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ማዕከላዊ ኮሚቴ በትናንትናና በዛሬ ቆይታው ለ9ኛ ድርጅታዊ ጉባዔ የሚቀርበውን ሪፖርትና የ2011 በጀት ዓመት ዕቅድን ተወያይቶበት አፅድቋል።
ኦህዴድ አሁን የተገኘውን ድል ሀገራዊ አድርጎ በመደመር መርህ አሸናፊ አስተሳሰብን እንዴት ማስቀጠል ይቻላል የሚለውን በስፋት ተወያይቶበታል።
ኮሚቴው ዛሬ በሎጎ ለውጥ፣ መዝሙር እና መተዳደሪያ ደንብ ላይ ውይይት እያደረገ ሲሆን፥ በእነዚህ እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ያስተላልፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽህፈት ቤት ማህበራዊ ድረ ገፁ እንዳሰፈረው ለ9ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ ከፍተኛ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንና ትልልቅ ውሳኔዎች ሊተላለፉበት እንደሚችሉ ጠቁሟል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *