Uncategorized

ቻይናውያን ሰላም አሰከባሪዎች ደቡብ ሱዳንን ለማገዝ ተዘጋጅተዋል፡፡

አርትስ 01/13/2010
ቻይና 268 ሰላም አስከባሪ ሀይሎችን ወደ ደቡብ ሱዳን ልትልክ መሆኑ ተሰምቷል፡፡
ሲጂቲኤን እንደዘገበው የሰላም አስከባሪ ወታደሮቹ በፈረንጆቹ መስከረም 11 እና 23 በሁለት የጉዞ ፕሮግራሞች ነው ወደ ጁባ የሚያቀኑት፡፡
ለአንድ ዓመት በደቡብ ሱዳን እንዲቆዩ ግዳጅ የተሰጣቸው እነዚህ የሰላም ልኡካን በመንገዶችና ድልደዮች ጥገና፣ በኤርፖርቶች እድሳት፣ በውሀ አቅርቦት ስራዎች እና በአጠቃላይ በኢንጂነሪንግ ዘርፍ ተሰማርተው የነዋሪዎቹን ችግር ለመፍታት የሚያስችል ተልዕኮ ነው የተሰጣቸው፡፡
ሰላም አስከባሪዎቹ ግዳጃቸውን በሚፈጽሙበት ወቅት ከወታደራዊ ተግባራቸው ጎን ለጎን የዲፕሎማሲ ፕሮቶኮሎችን እና የአካባቢውን ሁኔታ ከዓለም አቀፍ ህግ አንጻር የማጥናት ስራም ይጠብቃቸዋል ተብሏል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button