loading
አጥፍቶ ጠፊዎች ሞቃዲሾ ውስጥ አደጋ አድርሰዋል

አርትስ 05/13/2010
ከሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ በስተደቡብ ምስራቅ በምትገኘው የሆዳን ወረዳ ያልታወቁ ግለሰቦች ቦምብ የጫነ ተሸከርካሪ ይዘው ወደ አንድ የመንግስት ተቋም በመግባት ነው አደጋው አደጋውን ያደረሱት፡፡
ሮይተርስ እንደዘገበው ጥቃት አድራሾቹ ቦምቡን ከማፈንዳታቸው አስቀድመው በቦታው በነበሩ ሰዎች ላይ ተኩስ ከፍተውባቸው ነበር፡፡
የአካባቢው የፖሊስ አዛዥ በጥቃቱ ሰዎች መሞታቸውን ብናውቅም እስካሁን ቁጥራቸው ስንት እንደሆ ግን ዝርዝር መረጃ አልደረሰንም ብለዋል፡፡
በቦታው የነበሩ የዓይን እማኞች ደግሞ ቢያንስ ከአምስት ሰዎች በላይ በአምቡላንስ ወደ ሆስፒታል ሲወሰዱ ማየታቸውን ለሮይተርስ ተናግረዋል፡፡
እስካሁን ጥቃቱን ያደረሰኩት እኔ ነኝ የሚል አካል ባይኖርም ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ያለው አልሸባብ ሊሆን ይችላል የሚሉ ግምቶች እየተሰሙ ነው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *