Uncategorized

የአውሮፓ ህብረት የግብጽ የጅምላ የሞት ቅጣት ውሳኔ አሳስቦኛል አለ

አርትስ 02/01/2011
የግብጽ ፍርድ ቤት ሰሞኑን 75 ሰዎችን በሞት እንዲቀጡ መወሰኑን ተከትሎ ነው ህብረቱ ጉዳዩ አሳሳቢ መሆኑን የሚያመላክት በግለጫ ያወጣው፡፡
አናዶሉ የዜና ወኪል እንደዘገበው በተለይ የተከሳሾቹ የመብት ጥያቄዎች በአግባቡ የስነስርዓት ህጉን ጠብቀው ተስተናግደዋል የሚል እምነት የለኝም ብሏል ህብረቱ፡፡
በአወሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲና የደህንነት ጉዳዮች ከፍተኛ ተወካይ የሆኑት ፍሬዴሪካ ሞጎሮኒ የግብጽ ባለስልጣናት የራሳቸውን ህገ መንስግስትና እና አለም አቀፉን ህግ የማክበር ግዴታ አለባቸው ብለዋል፡፡
ግብጽ በበኩሏ በአንዲት ሉዓላዊት ሀገር የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባት ነው ስትል የህብረቱን መግለጫ አጣጥላዋለች፡፡
ግብጽ የፕሬዝዳንት ሞሀመድ ሙርሲ መንግስት በሀይል ከተወገደ አንስቶ ባለፉት አምስት ዓመታት በርካታ ሰዎችን በሞት ከመቅጣቷ በተጨማሪ በ10 ሽዎች የሚቆጠሩትን ማሰሯ ይነገራል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button