loading
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ እየሰጡ ነው፡፡

አርትስ 03/01/2011ዓ.ም
አሁን ላይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ አሸናፊ ነው፡፡ወንድም ወንድሙን ገፍቶ፣ገድሎ ማሸነፍ አይችልም፡፡ከተለያዩ ሀገሮች የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ገብተዋል፡፡ፓርቲዎቹ የገቡትም ሁላችንም አሸናፊ ስለሆንን ነው ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ሁሉም አሸናፊ የሚሆንበት አውድ እንዲፈጠር እንፈልጋለን፡፡ የአሸናፊዎች ስብስብ አሸናፊ አገር ይፈጥራል፡፡ አንዱ አሸናፊ አንዱ ተሸናፊ የሚሆንበት የፖለቲካ ስርዓት ኢትዮጵያ ውስጥ አያስፈልገንም ይበቃናል፡፡ ባንዲራ የሀሳብ መግለጫ የፓርቲዎች አርማ ነው፤ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ የሚፈልገው ከሆነ ባንዲራ በውይይት ሊቀየር ይችላል፣ በጉልበት ማስቀየር የሚፈልግ ካለ እሱ ጉልበት እንዳለው ሌለውን ጉልበት ስላለው አያዋጠም፡፡ የትኛውም ጫፍ የፖለቲካ አመለካከት ያለው የፖለቲካ ኃይል ካለ የኢትዮጵያ ህዝብ መቀበል አለበት፣ የማግለል ፖለቲካ መቆም አለበት፡፡ ወንድም ወንድሙን ገድሉ ማሸነፍ አይችልም፤ በሀሳብ ግን አሸናፊ መሆን ይቻላል ብለዋል፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *