loading
ፖሊስ የቀድሞው የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አብዲ መሀመድን ጨምሮ በሌሎች ተከሳሾች ላይ የጠየቀው ተጨማሪ 14 ቀን የምርምራ ጊዜ በፍርድ ቤቱ ተፈቀደለት

አርትስ 04/01/2011
የቀድሞው የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አብዲ መሐመድ ጨምሮ የሌሎች ተጠርጣሪዎችን ጉዳይ እየተመለከተ ያለው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ተረኛ ምድብ ችሎት በተጠርጣሪዎች የቀረቡትን አቤቱታ ሰምቷል።
ኢቢሲ እንደዘገበው ተጠርጣሪዎቹ ቤተሰብ እየጠየቅን አይደለም ምግብና ህክምናም በአግባቡ እያገኘን አይደለም የሚል ቅሬታ በጠበቆቻቸው በኩል አቅርበዋል።
መዝገቡ ሁሉንም ተጠርጣሪዎች በአንድ የያዘ ነው እንደኃላፊነታችን መጠን ሊለያይ ይገባል ሲሉም ፤የዋስትና መብታቸውም እንዲከበር ጠይቀዋል ።
ፍርድ ቤቱ የቀረቡትን ጉዳዮች በተመለከተ ለፖሊስ ተገቢውን ማስተካከያ እንዲያደረግ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
የተጠረጠሩበት ወንጀል የዋስትና መብት ስለማያሰጣቸው ይህን ጥያቄ ውድቅ በማድርግ ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል።
በመሆኑም ቀጣይ የቀጠሮ ጊዜ መስከረም 18 እንደሚሆን ፍርድቤቱ ወስኗል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *