loading
ከዚህ በኋላ መንግስት ነገሮችን በትዕግስት የሚያልፍበት ሁኔታ እንደማይኖር የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ ገለፁ

አርትስ 08/01/2011
የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ በቡራዩና አከባቢዋ በተፈጠረው ግጭት ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በቡራዩና አከባቢዋ በተፈጠረው ግጭት በህይወትና በንብረት ላይ በደረሰው ጉዳት ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማው እና
የኦሮሚያ ክልልም የተፈናቀሉ ወገኖችን ወደ ቀያቸው ለመመለስና መልሶ ለመቋቋም ሙሉ ኃላፊነት ወስዶ እንደሚሰራ አቶ ለማ ተናግረዋል።
ከዚህ በኋላ መንግስት ነገሮችን በትዕግስት የሚያልፍበት ሁኔታ እንደማይኖር እና እስከ አሁንም 300 አባወራዎችን ወደ ቀያቸው መመለስ እንደተቻለ ነው ርዕሰ መስተዳድሩ የተናገሩት፡፡
በግጭቱ እጃቸው አለበት የተባሉ ተጠርጣሪዎችና የተለያዩ የጦር መሳርያዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልፀዋል።
ግጭቱን ወደተለያዩ አከባቢዎች በተለይ ወደ አሰላ አከባቢ ለማስፋፋት ቢሞከርም ህብረተሰቡ ከፀጥታ ኃይሎች ጋር ባደረገው ትብብር መክሸፉን ጠቁመው ህብረተሰቡ አሁንም በተረጋጋ ስሜት በማስተዋል ሊንቀሳቀስ እንደሚገባም አሳስበዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *