EthiopiaSocial

በቡራዩ እና አካባቢው የተፈጠረዉን ችግር የሃይማኖት አባቶች እና ኦነግ አወገዙ

አርትስ 08/01/2011
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰጠችው መግለጫ ከዘመን መለወጫ በዓል ማግስት ይህ አፀያፊ ግድያና ዝርፊያ በዜጎች ላይ በመከሰቱ ቤተ ክርስቲያኗ እንዳዘነች በመግለፅ መንግስት በህገ ወጥ መንገድ በተለያየ ስም ተደራጅተው በሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ በፍጥነት ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ ፓትርያርክ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ጠይቀዋል፡፡
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀ መንበር አቶ ዳዉድ ኢብሳ መንግስት በቡራዩና በመዲናዋ በተፈጠሩ ችግሮች እጃቸዉ አለበት የተባሉ ተጠርጣሪዎችን አጣርቶ ማዉጣት አለበት ብለዋል፡፡
አቶ ዳዉድ ኢብሳ አክለዉም ድርጅታችን በሰላማዊ መንገድ በመታገል ላይ የሚገኝ በመሆኑ የድርጅቱ አባላትም የሌሎችን መብት በማይነካና ስነምግባር በተሞላበት መልኩ መንቀሳቀስ አለባቸው ሲሉ አሳስበዋል፡፡
የደኢህዴን ሊቀመንበር እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባዔ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል በበኩላቸዉ ከአሁን በኃላ የሚስተዋሉ የህግ ጥሰት እና የስርዓት አልበኝነት ባህሪ ያላቸው ድርጊቶችን አንታገስም ሲሉ ተናግረዋል።
በሀገሪቱ የሚገኙ 7 የፖለቲካ ፓርቲዎችም ሰሞኑን በአዲስ አበባና በሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች የተከሰቱ ግጭቶችን አውግዘዋል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button