loading
የ2011 የተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ጊዜ መራዘሙን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

አርትስ 08/01/11 ዓ.ም
የትምህርት ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ ሀረጓ ማሞ ለአርትስ ቲቪ እንደገለፁት ውይይት እየተደረገበት ባለው ረቂቅ የትምህርት ፍኖተ ካርታ ላይ ተጨማሪ የግብዓት ማሰባሰቢያ ውይይት እየተደረገ በመሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች ቀደም አስተላልፈውት የነበረው ጥሪ ወደ ተሸጋግሯል፡፡ የመግቢያ ጊዜው መራዘም አዲስም ሆነ ነባር ተማሪዎችን እንደሚመለከትም ወ/ሮ ሀረጓ ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም ዩኒቨርሲቲዎች ከመምሀራኖቻቸው እና ከአስተዳደር ሰራተኞቻቸው ጋር በረቂቅ ፍኖተ ካርታው ላይ ውይይት ካደረጉ በኋላ ከጥቅምት ወር መጀመሪያ አንስቶ የተማሪዎች መግቢያ የጥሪ መርሃ ግብር ይቀርባል ብለዋል፡፡
ሰፊ ውይይት ሲደረግበት የቆየው የፍኖተ ካርታ ረቂቅ ጥናት ግብዓት ማሰባሰብ ሂደት ሁሉንም ማህበረሰብ በሚያሳትፍ መልኩ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *