loading
አዲስ አበባ ወደ ቀድሞ መረጋጋቷ ብትመለስም የተንቀሳቃሽ ስልክ ኢንተርኔት አገልግሎት ግን እንደተቋረጠ ነዉ

አርትስ 08/01/2011
ቢቢሲ በልዩ ልዩ የከተማዋ አካባቢዎች ተንቀሳቅሶ መታዘብ እንደቻለው እስከዛሬ ማክሰኞ እኩለ ቀን ድረስ የንግድ መደብሮች፥ ምግብ ቤቶች እና ሌሎችም የአገልግሎት መስጫ ተቋማት ተከፍተዋል።
ካለፉት ሦስት ቀናት በተለየ በመንገዶች ላይ በርካታ ተሽከርካሪዎችን ሲንቀሳቀሱ ማስተዋል የሚቻል ሲሆን፥ ሠራተኞች እና ባለጉዳዮች በሰርክ እንቅስቃሴያቸው ተጠምደው ታይተዋል።
ይሁንና ከትናንትና አመሻሽ አንስቶ የተንቀሳቃሽ ስልክ የኢንተርኔት አገልግሎት በከተማዋ ተቋርጧል።በሌሎች በርካታ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ግን የተንቀሳቃሽ ስልክ የኢንተርኔት አገልግሎት በነበረው መልኩ መቀጠሉን አረጋግጬአለሁ ብሏል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *