loading
ዓላማ ያለዉ ትግል እንዲሳካ መደማመጥና በሰከነ ስሜት ማሰብ ይጠይቃል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፡፡

ጠቅላይ ሚኒሰትሩ ይህንን የተናገሩት በ9ነኛዉ የኦህዴድ ጉባኤ መክፈቻ ላይ በመገኘት ነዉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትግል መቀባበልንና አብሮ መስራትን እንዲሁም ዝግጁነትን ይጠይቃል፡፡ራሳችንን ጀምረን አንጨረስም ቅብብሎሹን መከተል ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡
ዶክተር አብይ ኦሮሞ ማስተዳደርም ሆነ መግዛት አይችልም ይባላል ግን ማስተዳደር ብቻ ሳይሆን መገንባትና መፍጠርም ይችላል ፡፡ኢትዮጵያን እንሰራታለን፤ህዝቦችዋን ብሄርና ብሄረሰቦችን ይዘን እንኖራለን ከዚህ የሚከለክለን የለም፡፡በሁሉም በኩል ዝግጅዎች ነን ብለዋል፡፡
የኦሮሞን ስም በማጣፍትና በመወንጀል የሚገኝ ትርፍ የለም፡፡የኦሮሞ ህዝብ በመረጠዉ ይተዳደራ ብለዋል፡፡
በኦሮሞ ህዝብ ስም መነገድ አስፈላጊ አይደለም ፤ክፍፍሎሹም ይበቃል አንድ ሁለትና ሶስት ፓርቲዎችም ለህዝባችን በቂ ናቸዉ ፡፡እንደባህላችንና ልማዳችን ተመካክረን ወደፊት እንሻገራለን፡፡እኛም ህዝብ ሲመርጣችሁ ወንበራችንን እንለቃለን፤እዚም እዛም አትበሉ ብለዋል፡፡
ለወጣቶቻችን የስራ እድል መፍጠር ግድ ይለናል፡፡የቤት ስራ ተሰጥቶናል በኢኮኖሚም ራስን መቻል ግድ ነዉ ብለዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *