loading
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከዚህ በኋላ በኦሮሞ ስም መነገድ አይቻልም ሲሉ አስጠነቀቁ

አርትስ 09/01/2011
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት በጅማ እየተካሄደ ባለው የኦህዴድ 9ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ መክፈቻ ላይ ነው፡፡
አስራ አምስት፣ ሃያ ሆኖ ለኦሮሞ መታገል አያስፈልግም፤ ከበዛ ሁለት ሶስት ፓርቲዎች ለኦሮሞ በቂ ናቸው ከጠላት ጋር ሆናችሁ የኦሮሞ ትግልን ወደኋላ ለመመለስ ያሰባችሁ ካላችሁ ከጠላት ለይተን አናያችሁም ከዚህ በኋላ በኦሮሞ ስም መነገድ አይቻልም ሲሉ ማስጠንቀቂያ አዘል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በተጨማሪም ኦሮሞ ማቀፍን፣ እናት የሌላቸውን ልጆች ማሳደግን ነው ያስተማረን፣ ኦሮሞ ከተዋጋ ያሸንፋል እንጂ ሰውን መግደልን አላስተማረንም ከሁሉም ኢትዮጵያ ህዝቦች ጋር በጋራ በአንድነት ተባብረን መስራት አለብን ብለዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *