loading
ሰሜን ኮሪያ የሚሳኤል ጣቢያዎቿን ለመዝጋት ተስማማች

አርትስ 10/01/2011
የሁለቱ ኮሪያዎች መሪዎች ፒዮንግያንግ ላይ ባደረጉት ውይይት ፕሬዝዳንት ኪም ጆንግ ኡን ቀጠናው ከኒውክሌር ስጋት ነፃ እነዲሆን ተግተን እንሰራለን ብለዋል፡፡
የሰሜን ኮሪያው ፕሬዝዳንት ሙን ጃይ ኢን ሰሜን ኮሪያ የቶንቻንግ ሪ የሚሳኤል ሙከራ ጣቢያን በቋሚነት ለመዝጋት ቃል ገብታለች ብለዋል፡፡
ፒዮንግያንግ ከዚህ በተጨማሪም የዮንግባዮን የኒውክሌር ማብላያ ጣቢያንም ለመዝጋት ተስማምታለች ፡፡
ቢቢሲ እንደዘገበው ሁለቱ መሪዎች የደረሱበት ስምምነት ለቀጣዩ የሰላም ሂደት አንድ ርምጃ ወደፊት የሚያራምድ ውጤት ነው፡፡
አሁን በቀጠናው እየታየ ያለው የመግባባት መንፈስ ለዘመናት ሰፍኖ የቆየውን ስጋትና አለመተማመን አስወግዶ ትብብርን ያጠናክራል ተስፋንም ፈንጥቋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *