loading
በቦሌ ክፍለ ከተማ ጤፍን ከባዕድ ነገር በመቀላቀል እንጀራ ጋግረው ሲሸጡ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

አርትስ 13/01/2011
ወረዳ 09 በተለምዶ “ዘይት መጭመቂያ” ተብሎ በሚጠራው ቦታ ጤፍን ከባዕድ ነገሮች ጋር በመቀላቀል እንጀራ ጋግረው ሲሸጡ የነበሩ ግለሰቦች በኅብረተሰቡ ጥቆማ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ወ/ት ወርቄና ትዕግስት አዳነ እንጀራ በመጋገር ለአንድ ወር ሠርተዋል፡፡ በቆይታቸውም 45 ኪሎ ግራም ጤፍን ከ100 ኪሎ ግራም ጀሶ ጋር በመቀላቀል ለባለሱቆች ያከፋፍላሉ፡፡ የማይሸጥና የተበላሸ እንጀራን ጀሶ ከተቀላቀለበት ጤፍ ጋር እንደገና በመቀላቀል ለጥቅም እንደሚውል አስረድተዋል፡፡
በኅብረተሰቡ ላይ ጥርጣሬ የሚፈጥሩ ነገሮችን ለፖሊስና ጉዳዩ ለሚመለከታቸው አካላት ጥቆማ መስጠት እንደሚገባ ረዳት ሳጅን ተክሌ በቀለ ጠቁመዋል፡፡
የቦሌ ክፍለ ከተማ ኮምንኬሽን ጽ/ቤት

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *