loading
በአዲግራት ለመስቀል ከ15ሺህ በላይ ችቦ ተዘጋጅቷል

አርትስ 16/01/2011
ከትናንት ጀምሮ በአዲግራት ከተማ በሃይማኖታዊና ባህላዊ ትውፊቶች እየተከበረ ያለው የመስቀል በዓል ዛሬ ወደ ተራራ ችቦ ይዞ በመውጣት የሚከበር ሲሆን በነገው ዕለት ደግሞ ደመራውን በመለኮስ የሚከበር ይሆናል፡፡ ከእስከዛሬው በተለየ ሁኔታ ትልልቅ ችቦዎች በወጣቶች የተዘጋጁ ሲሆን በብዛትም መጨመራቸውን ሰምተናል፡፡
ዘንድሮ የሚበራው ችቦ ከሌላው ጊዜ በተለየ በቁጥር ከ 15 ሺህ በላይ ሲሆን በቁመትም ረጃጅም ናቸው ተብሏል፡፡
22 ሜትር ቁመት ያለውና ግዙፍ የሆነውን መስቀል በፀሀይ ሀይል የሚሰራ መብራት ተገጥሞለት በአዲግራት ከተማ ቃን ዳዕሮ ተራራ ላይ እንደተተከለም የሚታወስ ነው፡፡
የደመራ እና መስቀል በዓል በአገራችን ከዛሬ ጀምሮ እስከ ነገ በተለያዩ ስነስርዓቶች ይከበራል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *