loading
ህወሃት በድርጅታዊ ጉባኤው ክልሉንና ሀገሪቱን የሚጠቅም ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ዶ/ር ደብረፅዮን ተናገሩ

አርትስ 16/01/2011
የድርጅቱ ሊቀመንበር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል 13ኛው የህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ /ህወሃት/ የድርጅታዊ ጉባኤ ዛሬ በመቐለ መካሄድ ሲጀምር ባደረጉት ንግግር ጉባዔዉ ታሪካዊ ውሳኔዎች የሚተላለፉበት እንደሚሆን ተስፋ አለኝ ብለዋል።
ጉባኤው የየክልሉ እና የሀገሪቱ ህዝብ ህዳሴ ማረጋገጫ በመሆኑ ጉዟችንን የተለየ ያደርገዋል ያሉት ዶክተር ደብረጽዮን፥ ለትግራይ ክልል እና ለኢትዮጵያ የሚጠቅሙ ውሳኔዎች እንደሚተላለፍበት ተናግረዋል።
ድርጅታዊ ጉባኤው ከውሳኔዎቹ በተጨማሪም አዳዲስ አመራሮች ወደ ሀላፊነት እንዲመጡ ለማድረግ ምርጫ እንደሚካሄድም ነው ዶክተር ደብረፅዮን በንግግራቸው የገለጹት፡፡
ድርጅቱ ከምንም በላይ እራሱን እየተፈተሸ ድክመቶቹን ያለ ምህረት እየታገለ ከነበረበት ችግር በመላቀቅ ለውጦችን ማምጣት የሚችል እንደሆነ ገልፀዋል።
አሁንም ከችግሮች ለመውጣት ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥልና በቀጣይ የመንግስትና የህዝብ መድረኮች በስፋት እንደሚኖሩ ነው ያስታወቁት።
ህውሃት ከሌሎች እህት ድርጅቶች ጋር በጋራ በመሆን ባደረገው ትግል አሁን ያለው ፓለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጥን ማስመዝገቡን ሊቀመንበሩ ጠቁመዋል።ይሁን እንጂ በውጭ እና በአገር ውስጥ ህገ መንግስቱንና መንግስትን ለመናድ እየተደረገ ያለውን ሙከራ እንደሚያወግዙም ዶክተር ደብረፅዮን በንግግራቸው አንስተዋል።
የዜጎች ህገመንግስታዊ መብት እየተጣሰ መጥቷል ያሉት ዶክተር ደብረፅዮን፥ ብሄርን ከብሄርን የሚያጋጩ ኃይሎችን ልንመክታቸው ይገባል ሲሉም ተናግረዋል።
በቀጣይም የህዝቦችን የእርስ በርስ ግንኙነት ለማጠናከር የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የሚያስችሉ ስራዎች እንደሚሰሩም አስታውቀዋል።
የኢትዮ ኤርትራን ግንኙነት በተመለከተ፥ የኢትዮጵያና ኤርትራ ህዝቦች ያለፈውን የችግር ግዜ ለመካስ የሚያስችሉ ስራዎች እንደሚሰሩም ገልፀዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *