loading
የባሕር ዳር ከተማ የእስልምና እምነት ተከታዮች ከክርስትያን ወንድሞቻቸው ጋር በመሆን ደመራ ደመሩ

አርትስ 16/01/2011
በባሕር ዳር ከተማ የእስልምና እምነት ተከታዮች የደመራ ስነ-ስርዓት መከወኛ ስፍራውን ከማጽዳት በተጨማሪ ለደመራ የሚያስፈልጉ እንጨት እና አደይ አበባ በማሰባሰብ ለክርስቲያን ወንድሞቻቸው የደመራ ቦታውን በጋራ አዘጋጅተዋል፡፡
የወጣቶች ተግባር በኢትዮጵያ ለዘመናት የቆየውን የሀይማኖት መቻቻል እና ሀገራዊ አንድነትን የሚያጠናክር ነው በማለት የአማራ ክልል ሀይማት ተቋማት ሰብሳቢ መላከ ሰላም ኤፍሬም ለአማራ ብዙሀን መገናኛ ድርጅት ተናግረዋል፡፡
መላከ ሰላም ኤፍሬም እንደሚሉት እንዲህ አይነት መረዳዳት የጋራ አብሮነታችን እና እሴቶቻችንን የሚያጠናክር ነው ፡፡
ትናንት በጎንደር የእስልምና ዕምነት ተከታዮች መሰል ተግባር ማከናወናቸው ይታወሳል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *