loading
የ2010 ዓ/ም የኢትዮጵያ ዋንጫ ዛሬ በሚደረግ የፍፃሜ ጨዋታ ይጠናቀቃል

አርትስ ሰፖርት19/01/2011
ውድድሩ ባለፈው አመት መጠናቀቅ ቢኖርበትም አንድ የሩብ ፍፃሜ ግጥሚያ እና የግማሽ ፍፃሜ እንዲሁም የፍፃሜ ጨዋታ ለዚህኛው አመት ተሸጋግሮ እነሆ ዛሬ መከላከያ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ በሚያደርጉት ጨዋታ መቋጫቸውን ያገኛል::
በግማሽ ፍፃሜው ኢትዮጵያ ቡናን በምንይሉ ወንድሙ የፍፁም ቅጣት ምት ጎል ያሸነፈው የጦሩ ቡድን መከላከያ: ድሉ ለዛሬው ግጥሚያ መነሣሣትን ይፈጥርለታል የተባለ ሲሆን ቡድኑ በአሰልጣኝ ስዮም ከበደ እየተመራ ጥሩ ጊዜ ላይ ይገኛል ::
ቅዱስ ጊዮርጊስ ጅማ አባ ጅፋር ከውድድሩ ራሱን ማግለሉን ተከትሎ በፎርፌ የፍፃሜ ተፋላሚ መሆኑን ያረጋገጠ ሲሆን የፕሪምየር ሊጉ አሸናፊ መሆን ሳይችል ቀርቶ ያመለጠውን የአፍሪካ መድረክ ተሳትፎ: በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ባይሆንም እንኳ በካፍ ኮንፌዴሬሽን ለመወዳደር በዚህ የፍፃሜ ጨዋታ ላይ አሸናፊ ሁኖ መውጣት ግድ ይለዋል።
ፈረሰኞቹ ለጨዋታው ጥሩ ዝግጅት እንዳደረጉ እና፤ ለብሔራዊ ቡድን ተጠርተው የነበሩት ተጨዋቾችም በመመለሳቸው ቡድኑ አሸናፊ እንዲሆን ያግዙታል ተብሏል::
የፍፃሜ ጨዋታው በ10:00 ስዓት ሀዋሳ ዓለም አቀፍ ስታድየም ላይ የሚደረግ ሲሆን አሸናፊው ቡድን ከዋንጫ እና ከገንዘብ ሽልማቱ በበለጠ በ2019 የካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ላይ ኢትየጵያን በመወከል የሚሳተፍ ይሆናል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *