loading
መከላከያ በ2019 የካፍ ኮንፌዴሬሽን ተሳታፊ መሆኑን አረጋገጠ

አርትስ ስፖርት 19/01/2011

የ2010 ዓ/ም የኢትዮጵያ ዋንጫ (የጥሎ ማለፍ ዋንጫ) በዛሬው ዕለት ፍፃሜውን ያገኘ ሲሆን በፍፃሜ ጨዋታው መከላከያ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ተገናኝተው፤ የጦሩ ቡድን በመለያ ምት 3 ለ 2 ማሸነፍ ችሏል፡፡

ሁለቱ ቡድኖች ሙሉ ጨዋታውን 0 ለ 0 ያጠናቀቁ ሲሆን በተሰጠው የመለያ ፍፁም ቅጣት ምት በአሰልጣኝ ስዩም ከበደ የሚመራው መከላከያ 3 ለ 2 በሆነ ውጤት በመርታት በውድድሩ በታሪኩ ለ14ኛ ጊዜ የኢትዮጵያ ዋንጫ ቻምፒዮን መሆን ችሏል ።

በመለያ ፍፁም ቅጣት ምቱ በቅዱስ ጊዮርጊስ በኩል አስቻለው ታመነ እና ጋዲሳ መብራቴ ማስቆጠር ቢችሉም በኃይሉ አሰፋ፣ ናትናኤል ዘለቀ እና ጌታነህ ከበደ ግን አምክነዋል፡፡

በመከላከያ በኩል ሽመልስ ተገኝ እና ዳዊት እስጢፋኖስ መለያ ምቶቹን ያመከኑ ተጫዋቾች ቢሆኑም ምንይሉ ወንድሙ፣ ተመስገን ገብረኪዳን እና አበበ ጥላሁን ቡድኑን ባለድል ያደረጉ ግቦች አስገኝተዋል፡፡

ይህን ተከትሎ መከላከያ ለውድድሩ የተዘጋጀውን ዋንጫ እና ገንዘብ ከመውሰዱ በተጨማሪ የ2019 የካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ተካፋይ መሆኑን አረጋግጧል፡፡

ባንፃሩ ፈረሰኞቹ ግን በ2011 ዓ.ም ከአህጉራዊ ውድድር ውጭ መሆናቸው እውን ሁኗል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *