loading
የወጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኢጋድ የሚኒስትሮች ካውንሰል ስብሰባ ለመሳተፍ ወደ ጅቡቲ ተጓዙ

የወጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኢጋድ የሚኒስትሮች ካውንሰል ስብሰባ ለመሳተፍ ወደ ጅቡቲ ተጓዙ
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ በ46ኛው የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) የሚኒስትሮች ካውንስል ስብሰባ ለመሳተፍ ወደ ጅቡቲ ተጉዘዋል።

ስብሳባው የካቲት 20 እና 21 ቀን 2011 ዓ.ም የአባል አገሮች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በተገኙበት በጅቡቲ የሚካሄድ ሲሆን የኢጋድ አሰራርን ለማዘመን በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት እንደሚያደርግ ይጠበቃል።

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ድርጅት ጀቡቲ፣ ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን እና ዩጋንዳን በአባልነት ያቀፈ ደርጅት ነው ።

የአሁኑ የሚኒስትሮች ካውንስል ስብሰባ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ የሚመራ እንደሆነ ተገልፃôል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *