loading
ከጉምሩክ አገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ በዘጠኝ ጉዳዮች ላይ የአሰራር ማሻሻያ ተደረገ

ከጉምሩክ አገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ በዘጠኝ ጉዳዮች ላይ የአሰራር ማሻሻያ ተደረገ
የጉምሩክ ኮሚሽን በዛሬው ዕለት ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር እየተካሄደ ባለው የምክክር መድረክ ላይ እንዳስታወቀው ከጉምሩክ አገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዞ የተንዛዙና ጊዜ የሚወስዱ የነበሩ ዘጠኝ ጉዳዮች ተለይተው ማሻሻያ ተደርጎባቸዋል፡፡
በተደረጉት የአሰራር ማሻሻያዎችም እስክ 48 ሰዓታት ጊዜን እና 3000 የአሜሪካ ዶላር ወጪ መቀነስ የሚያስችሉ እንደሆኑ ተገልጿል፡፡
የአሰራር ማሻሻያው የተደረገው ዕቃ ሳይደርስ የዕቃ አወጣጥ ስርዓት መፈፀም ዕቃዎች ከደረቅ ወደብ በባንክ ጋራንቲ ማስተናገድ፣ ለገቢና ወጪ ዕቃዎች የሚጠየቁ ሰነዶች መቀነስ፣ የአስገዳጅ ታሪፍ መረጃ አሰጣጥ፣ ቀለል ያለ የጉምሩክ ስነስርዓት አፈፃፀም፣ አዲሱ የኢትዮጵያ የጉምሩክ ስር አመራር ስርዓት፣ በወጪ እና ገቢ ዕቃዎች ላይ የስጋት ስራ አመራር ስርዓት ተግባራዊ ማድረግ እና ወጥነት ያለው የዕቃዎች ዋጋ መግለጫ ደረሰኝ ተግባራዊ ማድረግ በሚሉ ዘጠኝ ጉዳዮች ላይ ነው ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *