loading
አርትስ ዝክረ አደዋ‘’የሀዲያ ተወላጅ ፊታውራሪ ጌጃ ገርቦ’’

አርትስ ዝክረ አደዋ

የሀዲያ ተወላጅ ፊታውራሪ ጌጃ ገርቦ

ፊታውራሪ ጌጃ ገርቦ በደቡብ ኢትዮጵያ የሀዲያ ተወላጅ እና ልቅቦ ከተባለ  በሀዲያ ውስጥ ከሚገኝ ጎሳ የተገኙ ጀግና ናቸው፡፡

ፊት አውራሪ ጌጃ በአደዋ ዘመቻ የአጤ ምኒልክን መልዕክት ተከትለው የሀዲያን አከባቢ ወደ 5ሺ ጦር እየመሩ  በአድዋ ጦርነት በፊት አውራሪነት ከዘመቱ ጀግኖቻችን መካከል አንዱ ናቸው፡፡

የሐበሻ ጀብዱ የተደበቀው ማስታወሻ ላይ እንደሰፈረው ፊት አውራሪ ጌጃ ገሪቦ በአድዋ እና በማይጨው የፀረ ፋሺስት  ዘመቻ ላይም ትልቅ ሚና ነበራቸው፡፡
በ1888 ዓ.ም በአድዋ ጦርነት፣ በ1928 ዓ.ም ጣሊያን የቀድሞውን የአድዋ ሽንፈት ለመቀልበስ ኢትዮጲያን ድጋሚ በወረራት ወቅትም ፊት አውራሪ ጌጃ የሀዲያን ጦር እየመሩ ዘምተዋል፡፡

ፊት አውራሪ ጌጃ ገርቦ በዚህ መልክ  የሀዲያን ጦር እየመሩ  የአድዋ ጉዞ እስከሚጀመር ጦራቸውን አሰልፈው በአዲስ አበባ በጊዜአዊነት አርፈው ነበር፡፡

አዲስ አበባ ገብተው ጉዞ ወደ አድዋ እስኪ ጀመር በጊዚያዊነት ያረፉበት አካባቢም ‹‹የጌጃ ጦር›› ሰፈር ይባል ስለነበር ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ይህ አከባቢ ጌጃ ሰፈር በሚል ስያሜ ይጠራል፡፡

ጌጃ  ማለት የሀዲይኛ ቃል ሲሆን፤ ትርጓሜውም ጠብቆ ሲነበብ ፦ ትልቅ፣የከበረ፣ወፍራም ማለት ነው።
አላልተን ያነበብነው እንደሆን ደግሞ ፦ ደቦ፣በጋራ መስራት፣ መተጋገዝ እንደማለት ነው።

ፊት አውራሪ ጌጃ በተንቤን ግንባር በአውሮፕላን ቦምብ ጥቃት ነበር የተሰዉት፡፡

ስለእኚህ ጀግና በበቂ ሁኔታ ባለመፃፉ እና  የኢትዮጵያ ታሪክ ማስታወሻዎች ውስጥ ተመዝግቦ ባለመዘከራቸው ምክንያት ይህን ፅሁፍ ለማዘጋጀት እንኳ በቂ ምንጭ ለማግኘት ተቸግረናል ጀግኖቻችን ለሀገር ፣ዛሬ ለምንኩራራበት ነፃነት እራሳቸውን ገብረዋል እነርሱን መርሳት እንዴት ይቻለናል?

ክብር እና ሞገስ ለፊት አውራሪ ጌጃ ገርቦ!

በሰላም ገብሩ የተዘጋጀ

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *