loading
የአልጀሪያዊያን የተቃውሞ ሰልፍ መዘዙ ለጋዜጠኞች ተርፏል፡፡

የአልጀሪያዊያን የተቃውሞ ሰልፍ መዘዙ ለጋዜጠኞች ተርፏል፡፡

ፕሬዝዳንት አብደልአዚዝ ቡተፍሊካ በአልጀሪያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለአምስተኛ ጊዜ እወዳደራለሁ ማለታቸውን ተከትሎ በሀገሪቱ ከፍተኛ ቁጣ ተቀስቅሷል፡፡

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እና በሁኔታው የተበሳጩ በሽዎች የሚቆጠሩ አልጀሪያዊያን  ለተቃውሞ ሰልፍ አደባባይ መውጣት ከጀመሩ ውለው አድረዋል፡፡

ሮይተርስ ይህን ትእይንት ለመዘገብ የወጡ ጋዜጠኞችን ፖሊስ ይዞ አስሯቸዋል የሚል ዜና አስነብቧል፡፡

አሁን በሀገሪቱ የተቀሰቀሰውን አመፅ እንዲዘግቡ የተፈቀደላቸው በአልጀሪያ መንግስት የሚተዳደሩ የሚዲያ ተቋማት ብቻ መሆናቸውንም ዘገባው አስታውሷል፡፡

የአልጀሪያ መንግስት ሰልፉን ለመበተን በርካታ ፖሊሶችን በየከተሞቹ ያሰማራ ሲሆን ለተቃውሞ አደባባይ የወጡት ሰዎች ግን ቡተፍሊካ በቃቸው፣ ስልጣናቸውን ለሌሎች ያስረክቡ እያሉ በቁጣ ሲጮሁ ታይተዋል፡፡

ብዙዎቹ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ከ2013 ጀምሮ በጤና እክል ሳቢያ በተሸከርካሪ ወንበር የሚንቀሳቀሱት ፕሬዝዳንቱ ሀገር ለመምራ የሚያስችል ብቃት ላይ ገኙም ይላሉ፡፡

መንገሻ ዓለሙ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *