loading
ሩሲያ የገልፍ ሀገራት ህብረትን እንደምትደግፍ አስታወቀች፡፡

ሩሲያ የገልፍ ሀገራት ህብረትን እንደምትደግፍ አስታወቀች፡፡

የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ የገልፍ ሀገራት ጥምረት ተጠናክሮ ይቀጥል ዘንድ ኩዌት እያደረገች ያለችውን አስተዋጽኦ አድንቀው የሀገራቸው ድጋፍ እንደማይለያቸው ተናግረዋል፡፡

ሩሲያ በገልፍ ሀገራት  እና በኢራን መካከል ሰላም እና ፀጥታ ለማስፈን የበኩሏን እንደምትወጣ የተናገሩት ላቭሮቭ በሌላ በኩልም የፍልስጤምን ጉዳይ አንስተው እስካሁን  መፍትሔ ያላመጣውን የአሜሪካንን አደራዳሪነት  ዋጋ ቢስ ሲሉ ተችተውታል፡፡

የሩሲያው ኢንቨስትመንት ፈንድ ከኩዌት ኢንቨስትመንት ባለስልጣን ጋር የሁለት መቶ ሚሊዮን ዶላር መዋዕለ ንዋይ ስምምነት ተስማምተዋል፡፡

በተመሳሳይም ሀገራቱ በወታደራዊ ሃይል በትብብር ለመስራት ከስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡

የኩዌት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  ሼክ ሳባህ ካሊድ በሀገራቱ ሁለትዮሽ ጉዳዮች፣ በኢኮኖሚያዊ ትብብር ፣ በኢንቨስትመንት፣በፀጥታ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውጤታማ ምክክር ማድረጋቸውንም ተናግረዋል ሲል ሽንዋ ዘግቧል፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *